Celebrate Meskel

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረስዎ መልካም በዓል ለሁላችን።

በሀገረ አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ዘንድሮ በ2018 አከባበር

በሀገረ አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ዘንድሮ በ2018 ዓ.ም. እጅግ በደመቀ ሁኔታ ከ7 በላይ የሚሆኑ አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት ኑ የመስቀልን ደመራ በዓል ፥ ብርሃነ መስቀሉን በጋራ እናክብር የሚል ድንቅ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሜሪላንድ በሚገኘው በሐመረ ብርሃን መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በሚከወነው ታላቁ በዓላችን ላይ ይገኙ ዘንድ በክብር ተጋብዘዋል።

በዕለተ ቀኑ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ወይም September 26, 2025 ከቀኑ 3:00pm ሰዓት ጀምሮ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤት ክህነት ጽሕፈት ቤት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መምሪያ የበላይ ጠባቂ እና የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በዓሉ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

 ከየደብሩ የሚመጡ አባቶች ካህናት፥ ወንድሞች ዲያቆናት ፥የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና ምዕመናን በሙሉ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብራት ዕለቱን በደስታ ለማሳለፍ ተዘጋጅተዋል። እርስዎስ የት ኖት? የእርስዎ መገኘት ብቻ ሳይሆን ሌሎቹን ወደ ታላቁ የበረከት ስፍራ መጋበዝ ይገባዎታል። ለልጆችዎም የሚሆኑ መንፈሳዊ መርሐግብራት ስላሉን ይዘወ‍ኣቸው ይምጡ! ሀይማኖታዊ በዓላትዎን እያሳዩ በጎ ማንነትዎን ያውርሱ።

 ለፓርኪንግ አይጨነቁ ትልልቅ አውቶብሶች ተዘጋጅቷል።ሻትል ያመላልሳል፤ በሚከተለው እድራሻ :-

1/The Glenmont Metro station address is 12501 Georgia Avenue, Silver Spring, MD 20906.

2/Shady Grove Metro Station, 15903 Somerville Dr, Rockville, Maryland, 20855

 እንደሚቅርብዎት ይጠቀሙ።ሻትል አውቶብስቹ ይጠብቁዎታል።

በሥጋዎም በነፍስዎም ሀሴት ያገኙ ዘንድ ያስታውሱ በጎውን ማየት ለሚወዱ ሁሉ የብርሃን መንገድ ሆነው መልዕክቱን ያድርሱላቸው:-

 አድራሻ 4115 Muncaster Mill Rd, Rockville, MD 20853

 ኑ የመስቀል የደመራ በዓል በማክበር ብርክት እንቀበል።

በመስቀሉ ብርሃንም እንመላለስ።

The Hamere Berhan Kidus Yohannes Metmek Church in Maryland warmly invites all faithful and surrounding communities to join in the grand celebration of Meskel – the Finding of the True Cross. This sacred feast is one of the most significant in the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, symbolizing the triumph of faith and the enduring power of the Cross as a source of light, hope, and salvation.

This year’s celebration will take place on Friday, September 26, 2025, starting at 3:00 PM at Hamere Berhan Kidus Yohannes EOTC, located at 4115 Muncaster Mill Road, Rockville, MD. The day will be marked with vibrant liturgical services, joyful hymns, and the spirit of unity that has carried generations of believers.

To accommodate attendees, shuttle buses will run every 20 minutes starting at 3:30 PM from Glenmont Parking Garage (Silver Spring, MD) and Shady Grove Metro Station Park & Ride (Derwood, MD), ensuring convenient access for all.